

የሀዋሳ ታቦር 2ኛ እና መሰናዶ ት/ቤት የ11ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች በGIZ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋባዥነት የኮሌጃችን ኢንኩባሽን ሴንተር ጎበኙ ፡፡ በጉብኝቱን የተሳተፉት ሴት ተማሪዎች ከዚህ በፊት በTEVT ላይ የነበራቸዉን አመለካከት እንደ ተቀየረላቸዉና ከሴት አሰልጣኞቻችን የይቻላል መንፈስ እንደተፈጠረላቸዉ ኢንኩባሽን ሴንተር በሚሰጠዉ አገልግሎት ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን ያላቸዉን ፍላጎት ገልጸዉ ቀጣይ ትምህርታቸዉን ሲያጠናቀቁ ወደ ኮሌጃችን እንደምቀላቀሉ ተናግረዋሉ ፡፡
የGIZ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ተወካዮችም ኮሌጁ ባደረገላቸዉ አቀባበልና የተማሪዎች ደስተኛ መሆናቸዉን በማየት ከኮሌጃችን ጋር ያላቸዉን ግንኙት አጠናክሮ ለመቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡