በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሐዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በEASTRIP /East Africa Skill For Transformation And Regional Integration Project ድጋፍ እየተገነባ ያለ የልህቀት ማዕከል ግንባታ ያለበት ደረጃ በቢሮና ኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት ጉብኝት ተደርጓል። በጉብኝት ላይ የግንባታ መሀንዲስና አማካሪዎች የህንጻው ግንባ ያለበት ደረጃ አስመልክተው ገለጻ የሰጡ ስሆን፤የተወሰኑ መዘግየት ቢኖርም እየሄደ ያለበት ፍጥነት ጥሩ መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ ከሀገርቱም አልፎ ለአህጉሩ ያለው ፋይዳ የላቀ በመሆኑ በትኩረት እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁት የፕሮጀክቱ ሳይት መሀንዲስ፤በአየር ፀባይና በግንባታ ግባት እጥረት ከዚህ በፊት የተፈጠረው ችግር ሥራው በዚህ ግዜ 26 % መጠናቀቅ ስገባው በ18% ላይ  እንዲሆን ማድረጉንና የተፈጠረውን መዘገየት በፍጥነት ሰርተው ከታቀደው ግዜ በፊት ለማጠናቀቅ እየሠሩ እንደሚገኙ  ተናግሯል። የግንባታ ግባት በተለይ ስሚንቶ አቅርቦት ላይ ከበፊቱ መሻሻሎች ቢኖሩም፤አሁንም ፕሮጀክቱ በሚፈልገው ልክ እያገኙ ስላልሆነ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቋል። የክልሉ የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊዋ ተወካይ አቶ ቴዎድሮስ ጋዊዋ፤ኮንትራክተሩ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት ተረድተው በትኩረት ገንብተው ጨርሰው ለማስረከብ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው፤የክልሉ መንግስት በሚችለው ሁሉ ከጎናቸው ሆነው ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። ግንባታው በፍጥነት ተጠናቀው በተባለው ግዜ  ደርሶ የማህበረሰቡ ችግር እንዲፈታ እንፈልጋለን  ያለው አቶ ቴዎድሮስ ፤የጥራት ጉዳይም የማንደራደረው ቀይ መስመር በመሆኑ በጥንቃቄ እንዲሠራ በማለት አሳስቧል ።

1

2

3