Title
2014 የአዲስ ሠልጣኝ ምዝገባ
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘመናዊ የስልጠና መሳሪያዎችና ማሽነሪዎች በተደራጁ ወርክሾፖች እና በቂ ልምድ ባላቸው አሰልጣኝ መምህራን በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና በመስጠት ብቁ ቴክኒሺያኖችን በማፍራት ላይ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው ፡፡ ኮሌጁ በ2014 በጀት አመት ከደረጃ I – V በመደበኛና በማታው የስልጠና መረሃ ግብር ስልጠና የሚፈልጉ ዜጎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ትምህርታችሁን በ2011 " በ2013 እና በ2014 ዓ/ም ላጠናቀቃችሁ በተለያዩ የሙያ አይነቶች፡-
- በቴክስታይልና ጋርመንት ቴክኖሎጂ
- በሆቴልና ቱሪዝም
- በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
- በኤልክትሮ ቴክኖሎጂ
- በውኃ ቴክኖሎጂ
- በኮንስትራክ ቴክኖሎጂ
- በሮድ ኮንስትራክሽን
- በማኑፋክቸሪንግ
- በሌዘር ቴክኖሎጂ
- በአግሮ ፉድ ፕሮሰሲንግ
- በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ
- በሴክሬታሪያል ሣይንስ
- በአርበን ግሪነሪ
- በሰርቬይንግ
እና በሌሎች በርካታ ሙያዎች የአዲስ ሰልጣኞችን ምዝገባ የሚያካሄድ ሲሆን ከቀን 29/07/2014 እስከ ቀን 07/08/2014 ዓ.ም ድረስ በኮሌጃችን በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻችን ከሀዋሳ መምራን ትምህርት ኮሌጅ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡