Hawassi Politekinikete Kolleeje 2015 M.D 12kki Kifile gudde qajeelsha hasidhanno qansootira deerra mittuni ontu geeshsha ogimmate qajeelsha aate qixaawo gudde qajeelanno borressate hasidhanno. Konni daafira 12kki kifile guddine qajeelsha hasidhiniannir ballu Amaje barra 20/1015 M.D kayisine kollejete hoowo shiqqine borresama dandiitinannita egensiinseemmo.
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2015 ዓ/ም 12ኛ ክፍል አጠናቅቀው ሥልጠና የሚፈልጉ ዜጎችን ተቀብሎ ከደረጃ 1 እስከ 5 በመደበኛ እና በማታ ክፍለ ግዜ ለማሠልጠን ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ ስለሆነም በኮሌጃችን በተለያዩ ሙያዎች መሠልጠን የሚትፈልጉ ሁሉ ከየካቲት 20/2015 ዓ/ም ጀምሮ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት መመዝገብ የሚትችሉ መሆኑን እንግልፃለን፡፡

በሲዳማ ክልል በ2015 ዓ/ም ለቴክኖሎጂ ተወዳዳሪዎች የተደረግ የእውቅና ፕሮግራም(HPTC)

1

2

3

ሲዳማ ክልል በ2015 በሀገር አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በክህሎት ውድድረ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ላደረጉት አካላት በክልሉ መንግሥት በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተደረግ የእውቅና ፕሮግራም

HPTC hosts national EASTRIP monthly performance review meeting

HPTC hosts national EASTRIP monthly performance review meeting. MoLS team led by Honorable state minister Dr Teshale Berecha, all project implementing RFTIs throughout the country, NPCU, representatives from WB and regional bureau attended the meeting. Following the meeting, the team paid a site visit observe the construction progress.

h
e
e

 

EASTRIP /East Africa Skill For Transformation And Regional Integration Project ድጋፍ እየተገነባ ያለ የልህቀት ማዕከል ግንባታ ያለበት ደረጃ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሐዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በEASTRIP /East Africa Skill For Transformation And Regional Integration Project ድጋፍ እየተገነባ ያለ የልህቀት ማዕከል ግንባታ ያለበት ደረጃ በቢሮና ኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት ጉብኝት ተደርጓል። በጉብኝት ላይ የግንባታ መሀንዲስና አማካሪዎች የህንጻው ግንባ ያለበት ደረጃ አስመልክተው ገለጻ የሰጡ ስሆን፤የተወሰኑ መዘግየት ቢኖርም እየሄደ ያለበት ፍጥነት ጥሩ መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ ከሀገርቱም አልፎ ለአህጉሩ ያለው ፋይዳ የላቀ በመሆኑ በትኩረት እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁት የፕሮጀክቱ ሳይት መሀንዲስ፤በአየር ፀባይና በግንባታ ግባት እጥረት ከዚህ በፊት የተፈጠረው ችግር ሥራው በዚህ ግዜ 26 % መጠናቀቅ ስገባው በ18% ላይ  እንዲሆን ማድረጉንና የተፈጠረውን መዘገየት በፍጥነት ሰርተው ከታቀደው ግዜ በፊት ለማጠናቀቅ እየሠሩ እንደሚገኙ  ተናግሯል። የግንባታ ግባት በተለይ ስሚንቶ አቅርቦት ላይ ከበፊቱ መሻሻሎች ቢኖሩም፤አሁንም ፕሮጀክቱ በሚፈልገው ልክ እያገኙ ስላልሆነ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቋል። የክልሉ የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሃላፊዋ ተወካይ አቶ ቴዎድሮስ ጋዊዋ፤ኮንትራክተሩ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት ተረድተው በትኩረት ገንብተው ጨርሰው ለማስረከብ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው፤የክልሉ መንግስት በሚችለው ሁሉ ከጎናቸው ሆነው ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። ግንባታው በፍጥነት ተጠናቀው በተባለው ግዜ  ደርሶ የማህበረሰቡ ችግር እንዲፈታ እንፈልጋለን  ያለው አቶ ቴዎድሮስ ፤የጥራት ጉዳይም የማንደራደረው ቀይ መስመር በመሆኑ በጥንቃቄ እንዲሠራ በማለት አሳስቧል ።

1

2

3

 

የ2014 ዓ.ም አዲስ ሠልጣኞች ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን እና ምዝገባ የሚካሄድባቸው የሥልጠና ዘርፎች

Title
2014 የአዲስ ሠልጣኝ ምዝገባ

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘመናዊ የስልጠና መሳሪያዎችና ማሽነሪዎች በተደራጁ ወርክሾፖች እና በቂ ልምድ ባላቸው አሰልጣኝ መምህራን በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና በመስጠት ብቁ ቴክኒሺያኖችን በማፍራት ላይ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው ፡፡ ኮሌጁ በ2014 በጀት አመት ከደረጃ I – V በመደበኛና በማታው የስልጠና መረሃ ግብር ስልጠና የሚፈልጉ ዜጎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ትምህርታችሁን በ2011 " በ2013 እና በ2014 ዓ/ም ላጠናቀቃችሁ በተለያዩ የሙያ አይነቶች፡-

  • በቴክስታይልና ጋርመንት ቴክኖሎጂ
  • በሆቴልና ቱሪዝም
  • በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ
  • በኤልክትሮ ቴክኖሎጂ
  • በውኃ ቴክኖሎጂ
  • በኮንስትራክ ቴክኖሎጂ
  • በሮድ ኮንስትራክሽን
  • በማኑፋክቸሪንግ
  • በሌዘር ቴክኖሎጂ
  • በአግሮ ፉድ ፕሮሰሲንግ
  • በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ​​​​​​
  • በሴክሬታሪያል ሣይንስ
  • በአርበን ግሪነሪ
  • በሰርቬይንግ 

እና በሌሎች በርካታ ሙያዎች የአዲስ ሰልጣኞችን ምዝገባ የሚያካሄድ ሲሆን ከቀን 29/07/2014 እስከ ቀን 07/08/2014 ዓ.ም ድረስ በኮሌጃችን በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻችን ከሀዋሳ መምራን ትምህርት ኮሌጅ ወደ ሪፈራል ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ላይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Subscribe to